መዝሙረ ዳዊት. Chapter 134

1 የመዓረግ መዝሙር።1 እነሆ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ፥ በአምላካችን ቤት አደባባዬች የምትቆሙ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ።
2 በሌሊት በቤተ መቅደስ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፥ እግዚአብሔርንም ባርኩ።
3 ሰማይንና ምድርን የሠራ እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ።