መዝሙረ ዳዊት. Chapter 119
1 በመንገዳቸው ንጹሐን የሆኑ፥ በእግዚአብሔርም ሕግ የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።
2 ምስክሩን የሚፈልጉ፥ በፍጹም ልብ የሚሹት ምስጉኖች ናቸው፤
3 ዓመፅንም አያደርጉም፥ በመንገዶቹም ይሄዳሉ።
4 ትእዛዛትህን እጅግ እንጠብቅ ዘንድ አንተ አዘዝህ።
5 ሥርዓትህን ለመጠበቅ፤ መንገዶቼ ይቀኑ ዘንድ እወድድ ነበር።
6 ትእዛዝህን ሁሉ ስመለከት በዚያን ጊዜ አላፍርም።
7 አቤቱ፥ የጽድቅህን ፍርድ ስማር በቅን ልብ አመሰግንሃለሁ።
8 ሥርዓትህን እጠብቃለሁ፤ በፍጹም አትጣለኝ።ቤት
9 ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው።
10 በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ።
11 አንተ እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
12 አቤቱ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሥርዓትህን አስተምረኝ።
13 የአፍህን ፍርድ ሁሉ በከንፈሬ ነገርሁ።
14 እንደ ብልጥግና ሁሉ በምስክርህ መንገድ ደስ አለኝ።
15 ትእዛዝህን አሰላስላለሁ፥ መንገድህንም እፈልጋለሁ።
16 በትእዛዝህ ደስ ይለኛል፤ ቃልህንም አልረሳም።ጋሜል
17 ለባሪያህ መልካም አድርግ ሕያው እንድሆን፥ ቃልህንም እንድጠብቅ።
18 ዓይኖቼን ክፈት፥ ከሕግህም ተኣምራትህን አያለሁ።
19 እኔ በምድር እንግዳ ነኝ፤ ትእዛዛትህን ከእኔ አትሰውር።
20 ነፍሴ ሁልጊዜ ፍርድህን እጅግ ናፈቀች።
21 ከትእዛዛትህ የሳቱትን ትዕቢተኞችንና ርጉማንን ዘለፍህ።
22 ምስክርህን ፈልጌአለሁና። ስድብንና ነውርን ከእኔ አርቅ።
23 አለቆች ደግሞ ተቀምጠው እኔን አሙኝ፤ ባሪያህ ግን ሕግህን ያሰላስል ነበር።
24 ምስክርህም ተድላዬ ነው፥ ሥርዓትህም መካሪዬ ነው።ዳሌጥ
25 ነፍሴ ወደ ምድር ተጠጋች፤ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
26 መንገድህን ነገርሁ ሰማኸኝም፤ ሥርዓትህን አስተምረኝ።
27 የሥርዓትህን መንገድ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ተኣምራትህንም አሰላስላለሁ።
28 ከኀዘን የተነሣ ነፍሴ አንቀላፋች፤ በቃልህ አጠንክረኝ።
29 የዓመፅን መንገድ ከእኔ አርቅ፥ በሕግህም ማረኝ፤
30 የእውነትህን መንገድ መረጥሁ፥ ፍርድህንም አልረሳሁም።
31 አቤቱ፥ ምስክርህን ተጠጋሁ፤ አታሳፍረኝ።
32 ልቤን ባሰፋኸው ጊዜ፥ በትእዛዝህ መንገድ ሮጥሁ።ሄ
33 አቤቱ፥ የሥርዓትህን መንገድ አስተምረኝ፥ ሁልጊዜም እፈልገዋለሁ።
34 እንዳስተውል አድርገኝ፥ ሕግህንም እፈልጋለሁ፤ በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ።
35 እርስዋን ወድጃለሁና የትእዛዝህን መንገድ ምራኝ።
36 ልቤን ወደ ምስክርህ አዘንብል፥ ወደ ስስትም አይሁን።
37 ከንቱ ነገርን እንዳያዩ ዓይኖቼን መልስ፤ በመንገድህ ሕያው አድርገኝ።
38 እንዲፈራህ ባሪያህን በቃልህ አጽና።
39 ፍርድህ መልካም ናትና የተጠራጠርሁትን ስድብ ከእኔ አርቅ።
40 እነሆ፥ ትእዛዝህን ናፈቅሁ፤ በጽድቅህ ሕያው አድርገኝዋው
41 አቤቱ፥ እንደ ቃልህ፥ ምሕረትህና መድኃኒትህ ይምጡልኝ።
42 በቃልህ ታምኛለሁና ለሚሰድቡኝ በነገር እመልስላቸዋለሁ።
43 በፍርድህም ታምኛለሁና የእውነትን ቃል ከአፌ ፈጽመህ አታርቅ።
44 ለዘላለም ዓለም ሁልጊዜ ሕግህን እጠብቃለሁ።
45 ትእዛዛትህንም ፈልጌአለሁና አስፍቼ እሄዳለሁ።
46 በነገሥታት ፊት ምስክርህን እናገራለሁ፥ አላፍርምም፤
47 እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል።
48 እጆቼንም ወደ ወደድኋቸው ወደ ትእዛዛትህ አነሣለሁ፤ ሥርዓትህንም አሰላስላሁ።ዛይ
49 ለባሪያህ ተስፋ ያስደረግኸውን ቃልህን አስብ።
50 ቃልህ ሕያው አድርጎኛልና ይህች በመከራዬ ደስ አሰኘችኝ።
51 ትዕቢተኞች እጅግ ዐመፁ፤ እኔ ግን ከሕግህ አልራቅሁም።
52 ከጥንት የነበረውን ፍርድህን አሰብሁ፥ አቤቱ፥ ተጽናናሁም።
53 ሕግህን ከተዉ ከኃጢአተኞች የተነሣ ኅዘን ያዘኝ።
54 በእንግድነቴ አገር ሥርዓትህ መዝሙር ሆነችኝ።
55 አቤቱ፥ በሌሊት ስምህን አሰብሁ፥ ሕግህንም ጠበቅሁ።
56 ትእዛዛትህንም ፈልጌአለሁና፤ ይህች ሆነችልኝ።ሔት
57 እግዚአብሔር ክፍሌ ነው፤ ሕግህን እጠብቃለሁ አልሁ።
58 በፍጹም ልቤ ወደ ፊትህ ተማለልሁ፤ እንደ ቃልህ ማረኝ።
59 ስለ መንገዶችህ አሰብሁ፥ እግሬንም ወደ ምስክሮችህ መለስሁ።
60 ትእዛዝህን ለመጠበቅ ጨከንሁ አልዘገየሁምም።
61 የኃጥኣን ገመዶች ተተበተቡብኝ፤ ሕግህን ግን አልረሳሁም።
62 ስለ ጽድቅህ ፍርድ፥ በእኩለ ሌሊት አመሰግንህ ዘንድ እነሣለሁ።
63 እኔ ለሚፈሩህ ሁሉ፥ ትእዛዝህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ።
64 አቤቱ፥ ምሕረትህ በምድር ሁሉ ሞላች፤ ሥርዓትህን አስተምረኝ።ጤት
65 አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ለባሪያህ መልካም አደረግህ።
66 በትእዛዛትህ ታምኛለሁና መልካም ምክርና እውቀትን አስተምረኝ።
67 እኔ ሳልጨነቅ ሳትሁ፤ አሁን ግን ቃልህን ጠበቅሁ።
68 አቤቱ፥ አንተ ቸር ነህ፥ በቸርነትህም ሥርዓትህን አስተምረኝ።
69 የትዕቢተኞች ዓመፅ በላዬ በዛ፤ እኔ ግን በፍጹም ልቤ ትእዛዛትህን እፈልጋለሁ።
70 ልባቸው እንደ ወተት ረጋ፤ እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል።
71 ሥርዓትህን እማር ዘንድ ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።
72 ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል።ዮድ
73 እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ትእዛዛትህንም እማራለሁ።
74 በቃልህ ታምኛለሁና የሚፈሩህ እኔን አይተው ደስ ይላቸዋል።
75 አቤቱ፥ ፍርድህ ጽድቅ እንደ ሆነች፥ በእውነትህም እንዳስቸገርኸኝ አወቅሁ።
76 ምሕረትህ ለመጽናናቴ ትሁነኝ፥ እንደ ቃልህም ለባሪያህ ይሁነው።
77 ሕግህ ተድላዬ ናትና ቸርነትህ ትምጣልኝ፥ በሕይወትም ልኑር።
78 ትዕቢተኞች በዓመፅ ጠምመውብኛልና ይፈሩ፤ እኔ ግን በትእዛዝህ እጫወታለሁ።
79 የሚፈሩህና ምስክሮችህን የሚያውቁ ወደ እኔ ይመለሱ።
80 እንዳላፍር ልቤ በሥርዓትህ የቀና ይሁን።ካፍ
81 ነፍሴ መድኃኒትህን ናፈቀች፤ በቃልህም ታመንሁ።
82 መቼ ታጽናናኛለህ እያልሁ ዓይኖቼ ስለ ቃልህ ፈዘዙ።
83 በጢስ እንዳለ አቁማዳ ሆኛለሁና፤ ሥርዓትህን ግን አልረሳሁም።
84 የባሪያህ ዘመኖች ስንት ናቸው? በሚያሳድዱኝስ ላይ መቼ ትፈርድልኛለህ?
85 ኃጢአተኞች ጨዋታን ነገሩኝ፥ አቤቱ፥ እንደ ሕግህ ግን አይደለም።
86 ትእዛዛትህ ሁሉ እውነት ናቸው፤ በዓመፅ አሳድደውኛል፤ እርዳኝ።
87 ከምድር ሊያጠፉኝ ጥቂት ቀርቶአቸው ነበር፤ እኔ ግን ትእዛዛትህን አልተውሁም።
88 እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ፤ የአፍህንም ምስክር እጠብቃለሁ።ላሜድ
89 አቤቱ፥ ቃልህ በሰማይ ለዘላለም ይኖራል።
90 እውነትህ ለልጅ ልጅ ናት፤ ምድርን መሠረትሃት እርስዋም ትኖራለች።
91 ሁሉም ባሪያዎችህ ናቸውና ቀኑ በትእዛዝህ ይኖራል።
92 ሕግህ ተድላዬ ባይሆን፥ ቀድሞ በጐስቍልናዬ በጠፋሁ ነበር።
93 በእርሱ ሕያው አድርገኸኛልና ፍርድህን ለዘላለም አልረሳም።
94 እኔ የአንተ ነኝ፤ ፍርድህን ፈልጌአልሁና አድነኝ።
95 ኃጢአተኞች ያጠፉኝ ዘንድ ጠበቁኝ፤ ምስክርህን ግን መረመርሁ።
96 የሥራህን ሁሉ ፍጻሜ አየሁ፤ ትእዛዝህ ግን እጅግ ሰፊ ነው።ሜም
97 አቤቱ፥ ሕግህን እንደ ምን እጅግ ወደድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው።
98 ለዘላለም ለእኔ ነውና ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ።
99 ምስክርህ ትዝታዬ ነውና ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ።
100 ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ።
101 ቃልህን እጠብቅ ዘንድ ከክፉ መንገድ ሁሉ እግሬን ከለከልሁ።
102 አስተምረኸኛልና ከፍርድህ አልራቅሁም።
103 ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ።
104 ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ።ኖን
105 ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።
106 የጽድቅህን ፍርድ እጠብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸናሁም።
107 እጅግ ተቸገርሁ፤ አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
108 አቤቱ፥ ከአፌ የሚወጣውን ቃል ውደድ፥ ፍርድህንም አስተምረኝ።
109 ነፍሴ ሁልጊዜ በእጅህ ውስጥ ናት፤ ሕግህን ግን አልረሳሁም።
110 ኃጢአተኞች ወጥመድን ዘረጉብኝ፤ ከትእዛዝህ ግን አልሳትሁም።
111 የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘላለም ወረስሁ።
112 ለዘላለም ለፍጻሜውም ትእዛዝህን አደርግ ዘንድ ልቤን አዘነበልሁ።ሳምኬት
113 ዓመፀኞችን ጠላሁ፥ ሕግህን ግን ወደድሁ።
114 አንተ ረዳቴና መጠጊያዬ ነህ፥ በቃልህም ተማመንሁ።
115 እናንተ ኃጢአተኞች፥ ከእኔ ራቁ፥ የአምላኬንም ትእዛዝ ልፈልግ።
116 እንደ ቃልህ ደግፈኝ፥ ሕያውም እሆናለሁ። ከተስፋዬም አልፈር።
117 እርዳኝ እድናለሁም፥ ሁልጊዜም ሥርዓትህን እመረምራለሁ።
118 ምኞታቸው ዓመፃ ነውና ከሥርዓትህ የሚርቁትን ሁሉ አጐሳቈልሃቸው።
119 የምድርን ኃጢአተኞች ሁሉ እንደ ርኵሰት አጠፋሃቸው፤ ስለዚህ ምስክርህን ወደድሁ።
120 ሥጋዬ አንተን ከመፍራት የተነሣ ደንገጠ፤ ከፍርድህ የተነሣ ፈርቻለሁ።ዔ
121 ፍርድንና ጽድቅን ሠራሁ፤ ለሚያስጨንቁኝ አሳልፈህ አትስጠኝ።
122 ባሪያህን በመልካም ጠብቀው፤ ትዕቢተኞችም አይጋፉኝ።
123 ዓይኖቼ ለማዳንህ፥ ለጽድቅህም ቃል ፈዘዙ።
124 ለባሪያህ እንደ ምሕረትህ አድርግ፥ ሥርዓትህንም አስተምረኝ።
125 እኔ ባሪያህ ነኝ፤ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ምስክርህንም አውቃለሁ።
126 ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ ነው፥ ሕግህንም ሻሩት።
127 ስለዚህ ከወርቅና ከዕንቍ ይልቅ ትእዛዝህን ወደድሁ።