መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 26

1 ፤ ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ።
2 ፤ ኃይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው!ብርታት የሌለውን ክንድ ምንኛ አዳንኸው!
3 ፤ ጥበብስ የሌለውን ምንኛ መከርኸው!ብዙ እውቀትንስ ምንኛ ገለጥህለት!
4 ፤ ይህንስ ቃል በማን እርዳታ ተናገርህ?የማንስ መንፈስ ከአንተ ዘንድ ወጣ?
5 ፤ ሙታን ሰዎች ከውኆች በታች፥በውኆችም ውስጥ ከሚኖሩ በታች ይንቀጠቀጣሉ።
6 ፤ ሲኦል በፊቱ ራቁትዋን ናት፥ለጥፋትም መጋረጃ የለውም።
7 ፤ ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥ምድሪቱንም በታችዋ አንዳች አልባ ያንጠለጥላል።
8 ፤ ውኆችን በደመናዎቹ ውስጥ ያስራል፥ደመናይቱም ከታች አልተቀደደችም።
9 ፤ የዙፋኑን ፊት ይከድናል፥ደመናውንም ይዘረጋበታል።
10 ፤ ብርሃንና ጨለማ እስከሚለያዩበት ዳርቻ ድረስ፥በውኆች ፊት ላይ ድንበርን አደረገ።
11 ፤ የሰማይ አዕማድ ይንቀጠቀጣሉ፥ከተግሣጹም የተነሣ ይደነግጣሉ።
12 ፤ በኃይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል፥በማስተዋሉም ረዓብን ይመታል።
13 ፤ በመንፈሱ ሰማያት ውበትን አገኙ፥እጁም በራሪይቱን እባብ ወጋች።
14 ፤ እነሆ፥ ይህ የመንገዱ ዳርቻ ብቻ ነው፤ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው!የኃይሉንስ ነጐድጓድ ያስተውል ዘንድ ማን ይችላል?