መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 27

1 ፤ ኢዮብም ምሳሌውን ይመስል ዘንድ ደገመ፥ እንዲህም አለ።
2 ፤ ፍርዴን ያስወገደ ሕያው እግዚአብሔርን!ነፍሴንም መራራ ያደረገ ሁሉን የሚችል ሕያው አምላክን!
3 ፤ እስትንፋሴ በእኔ ውስጥ፥የእግዚአብሔርም መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ ገና ሳለ፥
4 ፤ ከንፈሬ ኃጢአትን አትናገርም፥አንደበቴም ሽንገላን አያወጣም።
5 ፤ እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፤እስክሞት ድረስ ፍጹምነቴን ከእኔ አላርቅም።
6 ፤ ጽድቄን እይዛለሁ እርሱንም አልተውም፤ከቀኖቼም ሁሉ ስለ አንዱ ልቤ አይዘልፈኝም።
7 ፤ ጠላቴ እንደ በደለኛ፥በእኔ ላይም የሚነሣ እንደ ኃጢአተኛ ይሁን።
8 ፤ እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በለየ ጊዜ፥የዝንጉ ሰው ተስፋው ምንድር ነው?
9 ፤ በውኑ መከራ በመጣበት ጊዜ፥እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን?
10 ፤ ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን?እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን?
11 ፤ እኔ ስለ እግዚአብሔር እጅ አስተምራችኋለሁ፤ሁሉን በሚችል አምላክ ዘንድ ያለውን አልሸሽግም።
12 ፤ እነሆ፥ ሁላችሁ አይታችኋል፤ስለ ምን ከንቱ ሆናችሁ?
13 ፤ ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ እድል ፈንታ፥ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ የሚቀበላት ርስት ናት፤
14 ፤ ልጆቹ ቢበዙ ለሰይፍ ይሆናሉ፤ዘሩም እንጀራን አይጠግብም።
15 ፤ ለእርሱም የቀሩት በቸነፈር ይቀበራሉ፤መበለቶቻቸውም አያለቅሱም።
16 ፤ እርሱ ብርን እንደ አፈር ቢከምር፥ልብስንም እንደ ጭቃ ቢያዘጋጅ፥
17 ፤ እርሱ ያዘጋጀው ይሆናል፥ ነገር ግን ጻድቅ ይለብሰዋል፤ብሩንም ንጹሐን ይከፋፈሉታል።
18 ፤ የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድር ይሠራል፥ጠባቂም እንደሚሠራው ጎጆ ነው።
19 ፤ ባለጠጋ ሆኖ ይተኛል፥ ዳግመኛም አይተኛም፤ዓይኑን ይከፍታል፥ እርሱም የለም።
20 ፤ ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ታገኘዋለች፤በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ትነጥቀዋለች።
21 ፤ የምሥራቅ ነፋስ ያነሣዋል፥ እርሱም ይሄዳል፤ከቦታውም ይጠርገዋል።
22 ፤ እርሱ ይጥልበታል፥ አይራራለትም፤ከእጁ ፈጥኖ መሸሽ ይወድዳል።
23 ፤ ሰው በእጁ ያጨበጭብበታል፤ከስፍራውም በፉጨት ያስወጡታል።