መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 25

1 ፤ ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ።
2 ፤ ገዢነትና መፈራት በእርሱ ዘንድ ናቸው፤በከፍታውም ሰላም አድራጊ ነው።
3 ፤ በውኑ ለሠራዊቶቹ ቍጥር አላቸውን?ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?
4 ፤ ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፥ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ እንዴት ይችላል?
5 ፤ እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለም፥ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።
6 ፤ ይልቁንስ ብስብስ የሆነ ሰው፥ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!