መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 12
1 ፤ ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ።
2 ፤ በእርግጥ እናንተ ዓይነተኞች ሰዎች ናቸሁ፤ጥበብም ከእናንተ ጋር ይሞታል።
3 ፤ ነገር ግን እኔ ደግሞ እንደ እናንተ ማስተዋል አለኝ፤ከእናንተም የማንስ አይደለሁም፤እንደዚህ ያለውን ነገር የማያውቅ ማን ነው?
4 ፤ እግዚአብሔርን የጠራሁ እርሱም የመለሰልኝ እኔለባልንጀራው መሳለቂያ እንደሚሆን ሰው ሆኛለሁ፤ጻድቅና ፍጹም ሰው መሳለቂያ ሆኖአል።
5 ፤ ተዘልሎ በሚቀመጥ ሰው አሳብ መከራ ይናቃል፤ነገር ግን እግሩን ሊያድጠው ተዘጋጅቶአል።
6 ፤ የቀማኞች ድንኳን በደኅንነት ይኖራል፥እግዚአብሔርንም የሚያስቈጡ ተዘልለው ተቀምጠዋል፤እግዚአብሔር ሁሉን በእጃቸው አምጥቶላቸዋል።
7 ፤ አሁን ግን እንስሶችን ጠይቅ፥ ያስተምሩህማል፤የሰማይንም ወፎች ጠይቅ፥ ይነግሩህማል።
8 ፤ ወይም ለምድር ተናገር፥ እርስዋም ታስተምርሃለች፤የባሕርም ዓሣዎች ይነግሩሃል።
9 ፤ የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገከእነዚህ ሁሉ የማያውቅ ማን ነው?
10 ፤ የሕያዋን ሁሉ ነፍስየሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናት።
11 ፤ ምላስ መብልን እንደሚቀምስ፥ጆሮ ቃልን የሚለይ አይደለምን?
12 ፤ በሽምግልና ጊዜ ጥበብ፥በዘመንስ ርዝመት ማስተዋል ይገኛል።
13 ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ፤ለእርሱ ምክርና ማስተዋል አለው።
14 ፤ እነሆ፥ ይፈርሳል፥ የፈረሰውም ተመልሶ አይሠራም፤በሰውም ቢዘጋበት የሚከፍትለት የለም።
15 ፤ እነሆ፥ ውኆቹን ይከለክላል፥ እነርሱም ይደርቃሉ፤እንደ ገና ይሰድዳቸዋል፥ ምድሪቱንም ይገለብጣሉ።
16 ፤ ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤የሚስተውና የሚያስተው ለእርሱ ናቸው።
17 ፤ መካሮችንም እንደ ዘረፋ ይወስዳቸዋል፥ፈራጆችንም ያሳብዳል።
18 ፤ የነገሥታትንም እስራት ይፈታል፥ወገባቸውንም በመታጠቂያ ያስራቸዋል።
19 ፤ ካህናትን እንደ ዘረፋ ይወስዳቸዋል፥ኃያላንንም ይገለብጣቸዋል።
20 ፤ ከታመኑ ሰዎችም ቋንቋን ያርቃል፥የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስድባቸዋል።
21 ፤ በአለቆች ላይ ንቀትን ያፈስሳል፥የብርቱዎችንም መታጠቂያ ያላላል።
22 ፤ ጥልቅ ነገር ከጨለማ ይገልጣል፥የሞትንም ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል።
23 ፤ አሕዛብን ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ እነርሱንም ያጠፋል፤አሕዛብንም ያሰፋል፥ እነርሱንም ያፈልሳቸዋል።
24 ፤ ከምድር አሕዛብ አለቆች ዘንድ ማስተዋልን ይወስዳል፥መንገድም በሌለበት በረሃ ያቅበዘብዛቸዋል።
25 ፤ ብርሃንም ሳይኖር በጨለማ ይርመሰመሳሉ፤እንደ ሰካራም ይቅበዘበዛሉ።