መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 3

1 ፤ ከዚያም በኋላ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ።
2 ፤ ኢዮብም መለሰ እንዲህ አለ።
3 ፤ ያ የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፥ያም። ወንድ ልጅ ተፀነሰ የተባለበት ሌሊት።
4 ፤ ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፥ብርሃንም አይብራበት።
5 ፤ ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው ገንዘብ ያድርጉት፤ዳመናም ይረፍበት፤የቀን ጨለማ ሁሉ ያስፈራው።
6 ፤ ያን ሌሊት ጨለማ ይያዘው፤በዓመቱ ቀኖች መካከል ደስ አይበለው፤በወሮች ውስጥ ገብቶ አይቈጠር።
7 ፤ እነሆ፥ ያ ሌሊት መካን ይሁን፤እልልታ አይግባበት።
8 ፤ ሌዋታንን ለማንቀሳቀስ የተዘጋጁቀኑን የሚረግሙ ይርገሙት።
9 ፤ አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፤ብርሃንን ቢጠባበቅ አያግኘው፥የንጋትንም ቅንድብ አይይ፤
10 ፤ የእናቴን ማኅፀን ደጅ አልዘጋምና፥መከራንም ከዓይኔ አልሰወረምና።
11 ፤ በማኅፀን ሳለሁ ስለ ምን አልሞትሁም?ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ፈጥኜ ስለ ምን አልጠፋሁም?
12 ፤ ጕልበቶች ስለ ምን ተቀበሉኝ?ጡትስ ስለ ምን ጠባሁ?
13 ፤ አሁን ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፤አንቀላፍቼ ባረፍሁ ነበር፤
14 ፤ የፈረሰውን ለራሳቸው ከሚሠሩትከምድር ነገሥታትና መካሮች ጋር፥
15 ፤ ወይም ቤታቸውን ብር ከሞሉወርቅም ካላቸው መኳንንት ጋር፥
16 ፤ ወይም እንደ ተቀበረ ጭንጋፍ፥ብርሃንም እንዳላዩ ሕፃናት በሆንሁ ነበር።
17 ፤ ክፉዎች በዚያ መናደዳቸውን ይተዋሉ፤በዚያም ደካሞች ያርፋሉ።
18 ፤ በዚያ ግዞተኞች በአንድነት ተዘልለው ተቀምጠዋል፤የአስጨናቂውን ድምፅ አይሰሙም።
19 ፤ ታናሽና ታላቅ በዚያ አሉ፤ባሪያም ከጌታው ነጻ ወጥቶአል።
20 ፤ በመከራ ላሉት ብርሃን፥ነፍሳቸው መራራ ለሆነችባቸው፥
21 ፤ የተሰወረ ሀብትን ከሚቈፍሩ ይልቅሞትን ለሚጠብቁ ለማያገኙትም፥
22 ፤ መቃብርን ባገኙ ጊዜበእልልታ ደስ ለሚላቸው፥ ሐሤትንም ለሚያደርጉሕይወት ስለ ምን ተሰጠ?
23 ፤ መንገዱ ለተሰወረበት ሰው፥እግዚአብሔርም በአጥር ላጠረውብርሃን ስለ ምን ተሰጠ?
24 ፤ ከእንጀራዬ በፊት ልቅሶዬ መጥቶአልና፥ጩኸቴም እንደ ውኃ ፈስሶአል።
25 ፤ የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና፥የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል።
26 ፤ ተዘልዬ አልተቀመጥሁም፥ አልተማመንሁም፥ አላረፍሁም፤ነገር ግን መከራ መጣብኝ።