መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 33
1 ፤ ነገር ግን፥ ኢዮብ ሆይ፥ ንግግሬን እንድትሰማ፥ቃሌንም ሁሉ እንድታደምጥ እለምንሃለሁ።
2 ፤ እነሆ፥ አፌን ከፍቻለሁ፥አንደበቴም በትናጋዬ ተናግሮአል።
3 ፤ ቃሌ የልቤን ቅንነት ያወጣል፤ከንፈሮቼም የሚያውቁትን በቅንነት ይናገራሉ።
4 ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።
5 ፤ ይቻልህ እንደ ሆነ መልስልኝ፤ቃልህንም አዘጋጅተህ በፊቴ ቁም።
6 ፤ እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት እኔ እንደ አንተ ነኝ፤እኔ ደግሞ ከጭቃ የተፈጠርሁ ነኝ።
7 ፤ እነሆ፥ ግርማዬ አታስፈራህምእጄም አትከብድብህም።
8 ፤ በጆሮዬ ተናግረሃል፥የቃልህንም ድምፅ ሰምቻለሁ፥ እንዲህም ብለሃል።
9 ፤ እኔ ያለ መተላለፍ ንጹሕ ነኝ፤ያለ ነውር ነኝ፥ ኃጢአትም የለብኝም፤
10 ፤ እነሆ፥ ምክንያት አግኝቶብኛል፥እንደ ጠላቱም ቈጥሮኛል፤
11 ፤ እግሬን በግንድ አጣበቀ፥መንገዴንም ሁሉ ተመለከተ።
12 ፤ እነሆ፥ አንተ በዚህ ጻድቅ አይደለህም፤እግዚአብሔር ከሰው ይበልጣል ብዬ እመልስልሃለሁ።
13 ፤ አንተ። ለቃሌ ሁሉ አይመልስልኝም ብለህ፥ስለ ምን ከእርሱ ጋር ትከራከራለህ?
14 ፤ እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፤ሰው ግን አያስተውለውም።
15 ፤ በሕልም፥ በሌሊት ራእይ፥አፍላ እንቅልፍ በሰዎች ላይ ሲወድቅ፥በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ፥
16 ፤ በዚያን ጊዜ የሰዎችን ጆሮ ይከፍታል፥በተግሣጹም ያስደነግጣቸዋል፥
17 ፤ ሰውን ከክፉ ሥራው ይመልሰው ዘንድከሰውም ትዕቢትን ይሰውር ዘንድ፤
18 ፤ ነፍሱን ከጕድጓድ፥በሰይፍም እንዳይጠፋ ሕይወቱን ይጠብቃል።
19 ፤ ደግሞ በአልጋ ላይ በደዌ ይገሥጸዋል፥አጥንቱንም ሁሉ ያደነዝዛል።
20 ፤ ሕይወቱም እንጀራን፥ነፍሱም ጣፋጭ መብልን ትጠላለች።
21 ፤ ሥጋው እስከማይታይ ድረስ ይሰለስላል፤ተሸፍኖ የነበረውም አጥንት ይገለጣል።
22 ፤ ነፍሱ ወደ ጕድጓዱ፥ሕይወቱም ወደሚገድሉአት ቀርባለች።
23 ፤ የቀናውን መንገድ ለሰው ያስታውቀው ዘንድ፥ከሺህ አንድ ሆኖ የሚተረጕም መልአክ ቢገኝለት፥
24 ፤ እየራራለት።ቤዛ አግኝቻለሁናወደ ጕድጓድ እንዳይወርድ አድነው ቢለው፥
25 ፤ ሥጋው እንደ ሕፃን ሥጋ ይለመልማል፤ወደ ጕብዝናውም ዘመን ይመለሳል።
26 ፤ ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥እርሱም ሞገስን ይሰጠዋልፊቱንም በደስታ ያሳየዋል፤ለሰውም ጽድቁን ይመልስለታል።
27 ፤ እርሱም በሰው ፊት እየዘመረ።እኔ በድያለሁ፥ ቅኑንም አጣምሜአለሁ፤የሚገባኝንም ብድራት አልተቀበልሁም፤
28 ፤ ነፍሴ ወደ ጕድጓድ እንዳትወርድ አድኖአታል፥ሕይወቴም ብርሃንን ታያለች ይላል።
29 ፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉሁለት ጊዜና ሦስት ጊዜ ከሰው ጋር ያደርጋል፤
30 ፤ ይህም ነፍሱን ከጕድጓድ ይመልስ ዘንድ፥በሕያዋንም ብርሃን ያበራ ዘንድ ነው።
31 ፤ ኢዮብ ሆይ፥ አድምጥ፥ እኔንም ስማ፤ዝም በል፥ እኔም እናገራለሁ።
32 ፤ ነገር ቢኖርህ መልስልኝ፤ትጸድቅ ዘንድ እወድዳለሁና ተናገር።
33 ፤ ያለዚያም እኔን ስማ፤ዝም በል፥ እኔም ጥበብን አስተምርሃለሁ።