መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 36

1 ፤ ኤሊሁም ደግሞ መለሰ እንዲህም አለ።
2 ፤ ገና ስለ እግዚአብሔር የሚነገር አለኝናጥቂት ቆየኝ፥ እኔም አስታውቅሃለሁ።
3 ፤ እውቀቴን ከሩቅ አመጣለሁ፥ፈጣሪዬንም። ጻድቅ ነው እላለሁ።
4 ፤ ቃሌ በእውነት ያለ ሐሰት ነው፤በእውቀትም ፍጹም የሆነ ከአንተ ጋር አለ።
5 ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም፤እርሱም በማስተዋል ብርታት ኃያል ነው።
6 ፤ እርሱ የበደለኞችን ሕይወት አያድንም፤ለችግረኞች ግን ፍርዱን ይሰጣል።
7 ፤ ዓይኑን ከጻድቃን ላይ አያርቅም፤ለዘላለምም ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፥እነርሱም ከፍ ከፍ ይላሉ።
8 ፤ በሰንሰለት ቢታሰሩ፥ወይም በችግር ገመድ ቢጠመዱ፥
9 ፤ ሥራቸውንና መተላለፋቸውንበትዕቢትም እንዳደረጉ ይናገራቸዋል።
10 ፤ ጆሮአቸውን ለተግሣጽ ይከፍተዋል፥ከኃጢአትም ይመለሱ ዘንድ ያዝዛቸዋል።
11 ፤ ቢሰሙ ቢያገለግሉትም፥ዕድሜአቸውን በልማት፥ዘመናቸውንም በተድላ ይፈጽማሉ።
12 ፤ ባይሰሙ ግን በሰይፍ ይጠፋሉ፥ያለ እውቀትም ይሞታሉ።
13 ፤ ዝንጉዎች ግን ቍጣን ያዘጋጃሉ፤እርሱም ባሰራቸው ጊዜ አይጮኹም።
14 ፤ በሕፃንነታቸው ሳሉ ይሞታሉ፥ሕይወታቸውም በሰዶማውያን መካከል ይጠፋል።
15 ፤ የተቸገረውን በችግሩ ያድነዋል፤በመከራም ጆሮአቸውን ይገልጣል።
16 ፤ እንዲሁም አንተን ከመከራችግር ወደሌለበት ወደ ሰፊ ስፍራ በወሰደህ ነበር፥በማዕድህ ላይ የተዘጋጀውም ስብ በሞላበት ነበር።
17 ፤ አንተ ግን በበደለኞች ፍርድ የተሞላህ ነህ፤ስለዚህ ፍርድና ብይን ይይዝሃል።
18 ፤ ቍጣ ለስድብ አያታልልህ፤የማማለጃም ብዛት ፈቀቅ አያድርግህ።
19 ፤ ባለጠግነትህ የኃይልህም ብርታት ሁሉያለ ችግር እንድትሆን ሊረዳህ ይችላልን?
20 ፤ ወገኖች ከስፍራቸው የሚወጡበትን ሌሊት አትመኝ።
21 ፤ ከመከራ ይልቅ ይህን መርጠሃልናኃጢአትን እንዳትመለከት ተጠንቀቅ።
22 ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር በኃይሉ ከፍ ያለውን ነገር ያደርጋል፤እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው?
23 ፤ መንገዱን ማን አዘዘለት?ወይስ። ኃጢአትን ሠርተሃል የሚለው ማን ነው?
24 ፤ ሰዎች የዘመሩትን ሥራውን ታከብር ዘንድ አስብ።
25 ፤ ሰዎች ሁሉ ተመልክተውታል፤ሰውም ከሩቅ ያየዋል።
26 ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም።የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም።
27 ፤ የውኃውን ነጠብጣብ ወደ ላይ ይስባል፥ዝናብም ከጉም ይንጠባጠባል፤
28 ፤ ደመናት ያዘንባሉ፥በሰዎችም ላይ በብዙ ያንጠባጥባሉ።
29 ፤ የደመናውንም መዘርጋት፥የማደሪያውንም ነጐድጓድ የሚያስተውል ማን ነው?
30 ፤ እነሆ፥ በዙሪያው ብርሃኑን ይዘረጋል፤የባሕሩንም ጥልቀት ይከድናል።
31 ፤ በእነዚህ በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤ብዙም ምግብ ይሰጣል።
32 ፤ እጆቹን በብርሃን ይሰውራል፥በጠላቱም ላይ ይወጣ ዘንድ ያዝዘዋል፤
33 ፤ የነጐድጓድ ድምፅ ስለ እርሱ ይናገራል፤እንስሶችም ደግሞ ስለሚመጣው ውሽንፍር ይጮኻሉ።