መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 37

1 ፤ ስለዚህም ልቤ ተንቀጠቀጠ፥ከስፍራውም ተንቀሳቀሰ።
2 ፤ የድምፁን መትመም ስሙ፥ከአፉም የሚወጣውን ጕርምርምታ አድምጡ።
3 ፤ እርሱን ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥ብርሃኑንም ወደ ምድር ዳርቻ ይሰድዳል።
4 ፤ በስተ ኋላው ድምፅ ይጮኻል፤በግርማውም ድምፅ ያንጐደጕዳል፤ድምፁም በተሰማ ጊዜመብረቁን አይከለክልም።
5 ፤ እግዚአብሔር በድምፁ ድንቅኛ ያንጐደጕዳል፤እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።
6 ፤ በረዶውንና ውሽንፍሩን ብርቱንም ዝናብ።በምድር ላይ ውደቁ ይላል።
7 ፤ ሰው ሁሉ ሥራውን ያውቅ ዘንድየሰውን ሁሉ እጅ ያትማል።
8 ፤ አውሬዎቹም ወደ ጫካው ይገባሉ፥በዋሾቻቸውም ይቀመጣሉ።
9 ፤ ከተሰወረ ማደሪያውም ዐውሎ ነፋስ፥ከሰሜንም ብርድ ይወጣል።
10 ፤ ከእግዚአብሔር እስትንፋስ ውርጭ ተሰጥቶአል፤የውኆችም ስፋት ይጠብባል።
11 ፤ የውኃውንም ሙላት በደመና ላይ ይጭናል፤የብርሃኑንም ደመና ይበታትናል፤
13 ፤ ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም ለምሕረት ቢሆን፥ሰው በሚኖርበት ዓለም ላይያዘዘውን ሁሉ ያደርግ ዘንድፈቃዱ ወደ መራችው ይዞራል።
14 ፤ ኢዮብ ሆይ፥ ይህን ስማ፤ቁም፥ የእግዚአብሔርንም ተአምራት አስብ።
15 ፤ በውኑ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያዝዛቸው፥የደመናውንም ብርሃን እንዴት እንደሚያበራ አውቀሃልን?
16 ፤ ወይስ የደመናውን ሚዛን፥ወይስ በእውቀት ፍጹም የሆነውን ተአምራት አውቀሃልን?
17 ፤ በደቡብ ነፋስ ምድር ጸጥ ባለች ጊዜ፥ልብስህ የሞቀች አንተ ሆይ፥
18 ፤ እንደ ቀለጠ መስተዋትብርቱ የሆኑትን ሰማያት ከእርሱ ጋር ልትዘረጋ ትችላለህን?
19 ፤ እኛ ከጨለማ የተነሣ በሥርዓት መናገር አንችልምናየምንለውን አስታውቀን።
20 ፤ ማንም በእርሱ ላይ ቢናገር ፈጽሞ ይዋጣልናእኔ እናገር ዘንድ ብወድድ ሰው ይነግረዋልን?
21 ፤ አሁንም ነፋስ አልፎ ካጠራቸው በኋላ፥ሰው በሰማያት የሚበራውን ብርሃን ሊመለከት አይችልም።
22 ፤ ከሰሜን ወርቅ የሚመስል ጌጠኛ ብርሃን ይወጣል፤በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስፈራ ግርማ አለ።
23 ፤ ሁሉን የሚችል አምላክን እናገኝ ዘንድ አንችልም፤በኃይል ታላቅ ነው፤በፍርድና በጽድቅም አያስጨንቅም።
24 ፤ ስለዚህ ሰዎች ይፈሩታል፤በልባቸውም ጠቢባን የሆኑትን ሁሉ አይመለከትም።