መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 34

1 ፤ ኤሊሁም ደግሞ መለሰ፥ እንዲህም አለ።
2 ፤ እናንተ ጥበበኞች፥ ቃሌን ስሙ፤እናንተም አዋቂዎች፥ ወደ እኔ አድምጡ።
3 ፤ ትናጋ መብልን እንደሚቀምስ፥ጆሮ ቃልን ትለያለችና።
4 ፤ ቅን የሆነውን ነገር እንምረጥ፤መልካሙንም ነገር በመካከላችን እንወቅ።
5 ፤ ኢዮብ። እኔ ጻድቅ ነኝ፥እግዚአብሔር ግን ፍርዴን አስወገደ፤
6 ፤ ምንም እውነተኛ ብሆን እንደ ውሸተኛ ተቈጠርሁ፤ምንም ባልበድል ቍስሌ የማይፈወስ ነው ብሎአል።
7 ፤8፤9፤ ኢዮብም። በእግዚአብሔር መደሰትለሰው ምንም አይጠቅምም ብሎአልናከበደለኞች ጋር የሚተባበር፥ክፉ ከሚያደርጉስ ጋር የሚሄድ፥መሳለቅን እንደ ውኃ የሚጠጣትእንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው?
10 ፤ ስለዚህ እናንተ አእምሮ ያላችሁ ሰዎች፥ ስሙኝ፤ክፋትን ያደርግ ዘንድ ከእግዚአብሔር፥በደልንም ይሠራ ዘንድ ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ።
11 ፤ ለሰው ሥራውን ይመልስለታል፥ሰውም እንደ መንገዱ ያገኝ ዘንድ ያደርጋል።
12 ፤ በእውነት እግዚአብሔር ክፉ አይሠራም፥ሁሉንም የሚችል አምላክ ፍርድን ጠማማ አያደርግም።
13 ፤ ምድርን አደራ የሰጠው ማን ነው?ዓለምንስ ሁሉ በእርሱ ላይ ያኖረ ማን ነው?
14 ፤ እርሱ ልቡን ወደ ራሱ ቢመልስ፥መንፈሱንና እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢሰበስብ፥
15 ፤ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በአንድነት ይጠፋል፥ሰውም ወደ አፈር ይመለሳል።
16 ፤ አስተዋይ ብትሆን ይህን ስማ፤የንግግሬንም ቃል አድመጥ።
17 ፤ በውኑ ጽድቅን የሚጠላ ይሠለጥናልን?ጻድቅና ኃያል የሆነውስ በደለኛ ታደርገዋለህን?
18 ፤ ማንም ሰው ንጉሡን። በደለኛ ነህ፥መኳንንቱንም። ክፉዎች ናችሁ ይላልን?
19 ፤ እነርሱ ሁሉ የእጁ ሥራ ናቸውናበአለቆች ፊት አያደላም፥ባለጠጋውንም ሰው ከድሀው ይበልጥ አይመለከትም።
20 ፤ እነርሱ በመንፈቀ ሌሊት በድንገት ይሞታሉ፤ሕዝቡ ተንቀጥቅጦ ያልፋል፥ኃያላንም ያለ እጅ ይነጠቃሉ።
21 ፤ ዓይኖቹ በሰው መንገድ ላይ ናቸው፥እርምጃውንም ሁሉ ያያል።
22 ፤ ኃጢአትን የሚሠሩ ይሰወሩበት ዘንድጨለማ ወይም የሞት ጥላ የለም።
23 ፤ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመፈራረድ እንዲመጣጊዜ አይወሰንለትም።
24 ፤ ታላላቆችን ያለ ምርመራ ይሰባብራል፥በእነርሱም ፋንታ ሌሎችን ያቆማል።
25 ፤ ሥራቸውን ያውቃል፤እንዲደቅቁም በሌሊት ይገለባብጣቸዋል።
26 ፤ ሰዎች እያዩ እንደ ክፉዎች ይመታቸዋል፤
28 ፤ የድሀውን ልቅሶ ወደ እርሱ ያደርሱ ዘንድ፥እርሱም የችግረኛውን ድምፅ ይሰማ ዘንድ፥እርሱን ከመከተል ፈቀቅ ብለዋልና፥ከመንገዱም ሁሉ አንዱን አልተመለከቱምና።
29 ፤ በሕዝብ ወይም በሰው ዘንድ ቢሆን፥እርሱ ቢያሳርፍ የሚፈርድ ማን ነው?ፊቱንስ ቢሰውር የሚያየው ማን ነው?
30 ፤ ይህም ዝንጉ ሰው እንዳይነግሥ፥ሕዝቡም የሚያጠምድ እንዳይኖር ነው።
31 ፤ እግዚአብሔርን። እኔ ሳልበድል ቅጣት ተቀበልሁ፤
32 ፤ የማላየውን ነገር አንተ አስተምረኝ፤ኃጢአትንም ሠርቼ እንደ ሆነ፥ደግሜ አልሠራም የሚለው ማን ነው?
33 ፤ በውኑ አንተ ጥለኸዋልናፍዳው አንተ እንደምትወድደው ይሆናልን?አንተ ትመርጣለህ እንጂ እኔ አይደለሁም፤ስለዚህ የምታውቀውን ተናገር።
34 ፤ የሚሰሙኝ ጥበበኞች ሁሉ፥አስተዋዮችም እንዲህ ይሉኛል።
35 ፤ ኢዮብ ያለ እውቀት ተናግሮአል፥ቃሉም በአእምሮ አይደለችም።
36 ፤ ኢዮብ እስከ ፍጻሜ ድረስ ምነው በተፈተነ ኖሮ!እርሱ እንደ ክፉዎች መልሶአልና፤
37 ፤ በኃጢአቱም ላይ ዓመፅን ጨምሮአልና፥በእኛም መካከል በእጁ ያጨበጭባልና፥ቃልንም በእግዚአብሔር ላይ ያበዛልና።