መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 35
1 ፤ ኤሊሁም ደግሞ መለሰ እንዲህም አለ።
2 ፤ ይህ ጽድቅ እንደ ሆነ ታስባለህን?ወይስ። በእግዚአብሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ ትላለህን?
3 ፤ አንተ። ምን ጥቅም አለህ?ኃጢአት ሠርቼ ከማገኘው ይልቅ ኃጢአት ባልሠራ ኖሮ ምን እጠቀማለሁ? ብለህ ጠይቀሃልና።
4 ፤ እኔ ለአንተና ከአንተ ጋር ላሉ ለባልንጀሮችህ እመልሳለሁ።
5 ፤ ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ እይ፤ከአንተም ከፍ ከፍ ያሉትን ደመናት ተመልከት።
6 ፤ ኃጢአት ብትሠራ ምን ትጐዳዋለህ?መተላለፍህስ ቢበዛ ምን ታደርገዋለህ?
7 ፤ ጻድቅስ ብትሆን ምን ትሰጠዋለህ?ወይስ ከእጅህ ምንን ይቀበላል?
8 ፤ እንደ አንተ ያለውን ሰው ክፋትህ ይጐዳዋል፤ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል።
9 ፤ ከግፍ ብዛት የተነሣ ሰዎች ይጮኻሉ፤ከኃያላንም ክንድ የተነሣ ለእርዳታ ይጠራሉ።
11 ፤ ነገር ግን። በሌሊት መዝሙርን የሚሰጥ፥ከምድርም እንስሶች ይልቅ የሚያስተምረንከሰማይም ወፎች ይልቅ ጥበበኞች የሚያደርገን፤ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ወዴት ነው? የሚል የለም።
12 ፤ በዚያ ስለ ክፉ ሰዎች ትዕቢት ይጮኻሉ፥እርሱ ግን አይመልስላቸውም።
13 ፤ በእውነት እግዚአብሔር ከንቱ ነገርን አይሰማም፥ሁሉን የሚችል አምላክም አይመለከተውም፤
14 ፤ ይልቁንም። አላየውም፤ነገሩ በእርሱ ፊት ነው፥ እኔም አጠብቀዋለሁ ስትል።
15 ፤ አሁን ግን በቍጣው አልጐበኘምና።በኃጢአት እጅግ አያስብም ትላለህ።
16 ፤ ስለዚህ ኢዮብ አፉን በከንቱ ይከፍታል፥ያለ እውቀትም ቃሉን ያበዛል።