መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 38
1 ፤ እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ።
2 ፤ ያለ እውቀት በሚነገር ቃልምክርን የሚያጨልም ይህ ማነው?
3 ፤ እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ፤እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ተናገረኝ።
4 ፤ ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ ወዴት ነበርህ?ታስተውል እንደ ሆንህ ተናገር።
5 ፤ ብታውቅስ መሠፈሪያዋን የወሰነ፥በላይዋስ የመለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው?
6 ፤7፤ አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥የእግዚአብሔርም ልጆች ሁሉ እልል ሲሉ፥መሠረቶችዋ በምን ላይ ተተክለው ነበር?የማዕዘንዋንስ ድንጋይ ያቆመ ማን ነው?
8 ፤ ከማኅፀን እንደሚወጣ በወጣ ጊዜባሕርን በመዝጊያዎች የዘጋ ማን ነው?
9 ፤ ደመናውን ለልብሱ፥ጨለማንም ለመጠቅለያው አደረግሁ፤
10 ፤ ድንበሩን በዙሪያው አድርጌ፥መወርወሪያዎቹንና መዝጊያዎቹን አኑሬ።
11 ፤ እስከዚህ ድረስ ድረሺ፥ አትለፊ፤በዚህም ለትዕቢተኛው ማዕበልሽ ገደብ ይሁን አልሁ።
13 ፤ የምድርን ዳርቻ ይይዝ ዘንድ፥ከእርስዋም በደለኞች ይናወጡ ዘንድ፥በውኑ ከተወለድህ ጀምሮ ማለዳን አዝዘሃልን?ለወገግታም ስፍራውን አስታወቀኸዋልን?
14 ፤ ጭቃ ከማኅተም በታች እንደሚለወጥ እንዲሁ እርስዋ ትለወጣለች፤ነገርም ሁሉ እንደ ልብስ ተቀልሞአል።
15 ፤ ከበደለኞች ብርሃናቸው ተከልክሎአል፥ከፍ ያለውም ክንድ ተሰብሮአል።
16 ፤ ወደ ባሕር ምንጭስ ውስጥ ገብተሃልን?በቀላዩስ መሠረት ውስጥ ተመላልሰሃልን?
17 ፤ የሞት በሮች ተገልጠውልሃልን?የሞትንስ ጥላ ደጆች አይተሃልን?
18 ፤ ምድርንስ በስፋትዋ አስተውለሃታልን?ሁሉን አውቀህ እንደ ሆነ ተናገር።
20 ፤ ወደ ዳርቻው ትነዳው ዘንድ፥ወደ ቤቱም የሚያደርሰውን ጐዳና ታውቅ ዘንድ፥የብርሃን መኖሪያ መንገድ የት ነው?የጨለማውስ ቦታ ወዴት አለ?
21 ፤ በዚያን ጊዜ ተወልደህ ነበርና፥የዕድሜህም ቍጥር ብዙ ነውና፤በእውነት አንተ ሳታውቅ አትቀርም።
22 ፤ በውኑ ወደ በረዶው ቤተ መዛግብት ገብተሃልን?የበረዶውንስ ቅንጣት ቤተ መዛግብት አይተሃልን?
23 ፤ ይኸውም ለመከራ ጊዜ ለሰልፍና ለጦርነት ቀን የጠበቅሁት ነው።
24 ፤ ብርሃንስ በምን መንገድ ይከፈላል?የምሥራቅስ ነፋስ በምድር ላይ እንዴት ይበተናል?
26 ፤ ባድማውንና ውድማውን እንዲያጠግብ፥
27 ፤ ሣሩንም እንዲያበቅል፥ማንም በሌለባት ምድር ላይ፥ሰውም በሌለባት ምድረ በዳ ላይ ዝናብን ያዘንብ ዘንድ፥ለፈሳሹ ውኃ መንዶልዶያውን፥ወይስ ለሚያንጐደጕድ መብረቅ መንገድን ያበጀ ማን ነው?
28 ፤ በውኑ ለዝናብ አባት አለውን?ወይስ የጠልን ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው?
29 ፤ በረዶስ ከማን ማኅፀን ወጣ?የሰማዩንስ አመዳይ ማን ወለደው?
30 ፤ ውኆች እንደ ድንጋይ ጠነከሩ፥የቀላዩም ፊት ረግቶአል።
31 ፤ በውኑ የሰባቱን ከዋክብት ዘለላ ታስር ዘንድ፥ወይስ ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ ትፈታ ዘንድ ትችላለህን?
32 ፤ ወይስ ማዛሮት የሚባሉትን ከዋክብት በጊዜያቸው ታወጣ ዘንድ፥ወይስ ድብ የሚባለውን ኮከብ ከልጆቹ ጋር ትመራ ዘንድ ትችላለህን?
33 ፤ የሰማይን ሥርዓት ታውቃለህን?በምድርስ ለይ እንዲሠለጥን ልታደርግ ትችላለህን?
34 ፤ የውኆች ብዛት ይሸፍንህ ዘንድቃልህን ወደ ደመናት ታነሣ ዘንድ ትችላለህን?
35 ፤ መብረቆች ሄደው። እነሆ፥ እዚህ አለን ይሉህ ዘንድልትልካቸው ትችላለህን?
36 ፤ በውስጡስ ጥበብን ያኖረ፥ለሰውስ ልብ ማስተዋልን የሰጠ ማን ነው?
38 ፤ የሰማይን ደመና በጥበቡ ሊቈጥር የሚችል ማን ነው?ትቢያ በተበጠበጠ ጊዜ፥ጓሎቹም በተጣበቁ ጊዜ፥የሰማይን ረዋት ሊያዘነብል የሚችል ማን ነው?
40 ፤ በዋሾቻቸው ውስጥ ተጋድመው፥በጫካም ውስጥ አድብተው ሳሉ፥ለአንበሳይቱ አደን ታድናለህን?የልጆችዋንስ ነፍስ ታጠግብ ዘንድ ትችላለህን?
41 ፤ ልጆቹ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፥የሚበሉትም አጥተው ሲቅበዘበዙ፥ለቍራ መብልን የሚሰጠው ማን ነው?