መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 17
1 ፤ መንፈሴ ደከመ፥ ዘመኔ አለቀ፥መቃብርም ተዘጋጅቶልኛል።
2 ፤ አላጋጮች በእኔ ዘንድ አሉ፥ዓይኔም በማስቈጣታቸው አደረች።
3 ፤ አሁንም አንተ መያዣ ሆነህ ተዋሰኝ፤ከእኔ ጋር አጋና የሚመታ ማን ነው?
4 ፤ ልባቸውም እንዳያስተውል ከልክለኸዋል፤ስለዚህ ከፍ ከፍ አታደርጋቸውም።
5 ፤ ለብዝበዛ ባልንጀሮቹን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥የልጆቹ ዓይን ይጨልማል።
6 ፤ ለሕዝብም ምሳሌ አደረገኝ፤በፊቱ ላይ ጺቅ እንደሚሉበት ሰው ሆንሁ።
7 ፤ ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘች፥ብልቶቼም ሁሉ እንደ ጥላ ሆኑ።
8 ፤ ቅኖች ሰዎች በዚህ ነገር ይደነቃሉ፥ንጹሕም በዝንጉው ላይ ይበሳጫል።
9 ፤ ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠነክራል፥እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።
10 ፤ ነገር ግን እናንተ ሁሉ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ፤በእናንተም ዘንድ ብልሃተኛ አላገኝም።
11 ፤ ዕድሜዬ አለፈች፤አሳቤና የልቤ መሣርያ ተቈረጠ።
12 ፤ ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤ብርሃኑም ወደ ጨለማ የቀረበ ይመስላቸዋል።
13 ፤ ተስፋ ባደርግ ሲኦል ቤቴ ናት፤ምንጣፌንም በጨለማ ዘርግቻለሁ።
14 ፤ መበስበስን። አንተ አባቴ ነህ፤ትልንም። አንቺ እናቴ እኅቴም ነሽ ብያለሁ።
15 ፤ እንግዲህ ተስፋዬ ወዴት ነው?ተስፋዬንስ የሚያይ ማን ነው?
16 ፤ አብረን በመሬት ውስጥ ስናርፍ፥ወደ ሲኦል ይወርዳል።