መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 19
1 ፤ ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ።
2 ፤ ነፍሴን የምትነዘንዙ፥በቃልስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው?
3 ፤ ይኸው ስትሰድቡኝ አሥር ጊዜ ነው፤ስታሻክሩኝም አላፈራችሁም።
4 ፤ በእውነትም የሳትሁ እንደ ሆነ፥ስሕተቴ ከእኔ ጋር ትኖራለች።
5 ፤ በእውነትም ብትጓደዱብኝ፥መዋረዴን በእኔ ላይ ብትከራከሩ፥
6 ፤ እንግዲህ እግዚአብሔር እንደ ገለበጠኝ፥በመረቡም እንደ ከበበኝ እወቁ።
7 ፤ እነሆ፥ ስለ ተደረገብኝ ግፍ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፤አሰምቼም ብጠራ ፍርድ የለኝም።
8 ፤ እንዳላልፍ መንገዴን ዘግቶታል፥በጎዳናዬም ጨለማ አኑሮበታል።
9 ፤ ክብሬን ገፈፈኝ፥ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወሰደ።
10 ፤ በዚህና በዚያም አፈረሰኝ፥ እኔም ሄድሁ፤ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቀለው፤
11 ፤ ቍጣውንም አነደደብኝ፥እንደ ጠላቱም ቈጠረኝ።
12 ፤ ሠራዊቱ አብረው መጡ፥መንገዳቸውንም በላዬ አዘጋጁ፥በድንኳኔም ዙሪያ ሰፈሩ።
13 ፤ ወንድሞቼን ከእኔ ዘንድ አራቀ፥የሚያውቁኝም አጥብቀው ተለዩኝ።
14 ፤ ዘመዶቼ ተቋረጡ፥ወዳጆቼም ረሱኝ።
15 ፤ ቤተ ሰቦቼና ሴቶች ባሪያዎቼ እንደ መጻተኛ ቈጠሩኝ፤በዓይናቸውም እንደ እንግዳ ሆንሁ።
16 ፤ ባሪያዬን ብጠራ፥ በአፌም ባቈላምጥ አይመልስልኝም።
17 ፤ ሚስቴ እስትንፋሴን ጠላች፥የእናቴም ማኅፀን ልጆች ልመናዬን ጠሉ።
18 ፤ ሕፃናቶች እንኳ አጠቁኝ፤ብነሣም በእኔ ላይ ይናገራሉ።
19 ፤ አማካሪዎቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤እኔ የምወድዳቸው በላዬ ተገለበጡ።
20 ፤ አጥንቴ ከቁርበቴና ከሥጋዬ ጋር ተጣበቀ፤ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።
21 ፤ እናንተ ወዳጆቼ ሆይ፥ ማሩኝ፤የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና ማሩኝ።
22 ፤ ስለ ምን እናንተ እንደ እግዚአብሔር ታሳድዱኛላችሁ?ከሥጋዬስ ስለ ምን አትጠግቡም?
23 ፤ ምነው አሁን ቃሌ ቢጻፍ!ምነው በመጽሐፍ ውስጥ ቢታተም!
24 ፤ ምነው በብረት ብርና በእርሳስበዓለቱ ላይ ለዘላለም ቢቀረጽ!
25 ፤ እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም፥
26 ፤ ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ።
27 ፤ እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ዓይኖቼም ይመለከቱታል፥ከእኔም ሌላ አይደለም።ልቤ በመናፈቅ ዝሎአል።
28 ፤ በእውነት። እንዴት እናሳድደዋለን?የነገሩ ሥር በእርሱ ዘንድ ተገኝቶአል ብትሉ፥
29 ፤ ፍርድ እንዳለ ታውቁ ዘንድቍጣ የሰይፍን ቅጣት ያመጣልናከሰይፍ ፍሩ።