መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 9
1 ፤ ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ።
2 ፤ በእውነት እንዲህ እንደ ሆነ አወቅሁ፤ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ መሆን እንዴት ይችላል?
3 ፤ ከእርሱ ጋር ይከራከር ዘንድ ቢወድድ፥ከሺህ ነገር አንዱን መመለስ አይችልም።
4 ፤ ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፤ደፍሮትስ በደኅና የሄደ ማን ነው?
5 ፤ ተራሮችን ይነቅላል፤ አያውቁትም፤በቍጣውም ይገለብጣቸዋል።
6 ፤ ምድርን ከስፍራው ያናውጣታል፥ምሰሶችዋም ይንቀጠቀጣሉ።
7 ፤ ፀሐይን ያዝዛታል፥ አትወጣምም፤ከዋክብትንም ያትማል።
8 ፤ ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል፥በባሕሩም ማዕበል ላይ ይረግጣል።
9 ፤ ድብ የሚባለውን ኮከብና ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥በደቡብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ማደርያዎች ሠርቶአል።
10 ፤ የማይመረመረውን ታላላቅ ነገር፥የማይቈጠረውንም ተአምራት ያደርጋል።
11 ፤ እነሆ፥ ቢመጣብኝ አላየውም፤ቢያልፍብኝም አላውቀውም።
12 ፤ እነሆ፥ ፈጥኖ ቢነጥቅ የሚከለክለው ማን ነው?እርሱንስ። ምን ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?
13 ፤ እግዚአብሔር ቍጣውን አይመልስም፤ከእርሱ በታች ረዓብን የሚረዱ ይዋረዳሉ።
14 ፤ ይልቁንስ እመልስለት ዘንድ፥ቃሌንስ በፊቱ እመርጥ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?
15 ፤ ጻድቅ ብሆን ኖሮ አልመልስለትም ነበር፤ወደ ፈራጄም እለምን ነበር።
16 ፤ ብጠራው እርሱም ቢመልስልኝ ኖሮ፥ቃሌን እንደ ሰማ አላምንም ነበር።
17 ፤ በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፥ቍስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛል።
18 ፤ እተነፍስ ዘንድ አይተወኝም፥ነገር ግን መራራን ነገር አጥግቦኛል።
19 ፤ የኃይል ነገር ቢሆን እርሱ ኃያል ነው፤የፍርድ ነገር ቢሆን። ጊዜን ወሳኙ ማን ነው? ይላል።
20 ፤ ጻድቅ ብሆን አፌ ይወቅሰኛል፤ፍጹምም ብሆን ጠማማ ያደርገኛል።
21 ፤ ፍጹም ነኝ ራሴንም አልመለከትም፤ሕይወቴንም እንቃታለሁ።
22 ፤ ይህ ሁሉ አንድ ነው፤ ስለዚህ።ፍጹማንንና ክፉዎችን ያጠፋል እላለሁ።
23 ፤ መቅሠፍቱ ፈጥኖ ቢገድል፥በንጹሐን ፈተና ይሳለቃል።
24 ፤ ምድር በኃጥአን እጅ ተሰጥታለች፤የፈራጆችዋን ፊት ሸፍኖአል፤እርሱ ካልሆነ ማን ነው?
25 ፤ ዘመኔ ከሚሮጥ ሰው ይልቅ ይፈጥናል፤ይሸሻል፥ መልካምንም አያይም።
26 ፤ የደንገል ታንኳ እንደሚፈጥን፥ንስርም ወደ ንጥቂያው እንደሚበርር ያልፋል።
27 ፤ እኔ። የኀዘን እንጕርጕሮዬን እረሳለሁ፤ፊቴን መልሼ እጽናናለሁ ብል፥
28 ፤ ንጹሕ እንደማታደርገኝ እኔ አውቃለሁናከመከራዬ ሁሉ እፈራለሁ።
29 ፤ በደለኛ እንደሚሆን ሰው እሆናለሁ፤ስለ ምንስ በከንቱ እደክማለሁ?
30 ፤ በአመዳይ ውስጥ ብታጠብ፥እጆቼንም እጅግ ባነጻ፥
31 ፤ በአዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ፥ልብሴም ይጸየፈኛል።
32 ፤ እንድመልስለት አብረን ወደ ፍርድ እንገባ ዘንድ፥እርሱ እንደ እኔ ሰው አይደለም።
33 ፤ እጁን በሁለታችን ላይ የሚያኖር ዳኛበመካከላችን ምነው በተገኘ!
34 ፤ በትሩን ከእኔ ላይ ያርቅ፥ግርማውም አያስፈራኝ፤
35 ፤ እናገርም ነበር፥ አልፈራውምም ነበር፤በራሴ እንዲህ አይደለሁምና።