መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 15
1 ፤ ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ እንዲህም አለ።
2 ፤ በውኑ ጠቢብ ሰው እንደ ንፋስ በሆነ እውቀት ይመልሳልን?በሆዱስ የምሥራቅን ነፋስ ይሞላልን?
3 ፤ ከማይረባ ነገር፥ወይስ ከማይጠቅም ንግግር ጋር ይዋቀሳልን?
4 ፤ አንተም እግዚአብሔርን መፍራት ታፈርሳለህ፤በእግዚአብሔር ፊት አምልኮን ታስቀራለህ።
5 ፤ በደልህ አፍህን ያስተምረዋል፥የተንኰለኞችንም አንደበት ትመርጣለህ።
6 ፤ የሚፈርድብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።ከንፈሮችህም ይመሰክሩብሃል።
7 ፤ በውኑ መጀመሪያ የተወለድህ ሰው አንተ ነህን?ወይስ ከተራሮች በፊት ተፀነስህን?
8 ፤ የእግዚአብሔርንስ ምሥጢር ሰምተሃልን?ወይስ ጥበብን ለብቻህ አድርገሃልን?
9 ፤ እኛ የማናውቀውን አንተ የምታወቀው ምንድር ነው?ከእኛ ዘንድስ የሌለው የምታስተውለው ምንድር ነው?
10 ፤ በዕድሜ ከአባትህ የሚበልጡሽበትም ያላቸው ሽማግሌዎችም ከእኛ ጋር አሉ።
11 ፤ በውኑ የእግዚአብሔር ማጽናናት፥በየውሃትም የተነገረህ ቃል ጥቂት ነውን?
12 ፤ ልብህስ ለምን ይወስድሃል?ዓይኖችህስ ለምን ይገለምጣሉ?
13 ፤ በእግዚአብሔር ላይ መንፈስህን እስከ ማንሣት ደርሰህ፤ይህንም ቃል ከአፍህ እስከ ማውጣት ደርሰህ።
14 ፤ ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድር ነው?ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ምንድር ነው?
15 ፤ እነሆ፥ በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም፤ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።
16 ፤ ይልቁንስ አስጸያፊና የረከሰ፥ኃጢአትንም እንደ ውኃ የሚጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?
18 ፤ ምድሪቱ ለብቻቸው ተሰጥታ የነበረች፥
19 ፤ በመካከላቸውም እንግዳ ያልገባባቸው ጠቢባን።ከአባቶቻቸው ተቀብለው የተናገሩትን ያልሸሸጉትንም፥እገልጥልሃለሁ፥ ስማኝ፤ ያየሁትንም እነግርሃለሁ።
20 ፤ ክፉ ሰው ዕድሜውን ሙሉ፥ከግፈኛ በተመደቡለት በዓመታት ሁሉ በሕመም ይጣጣራል።
21 ፤ የሚያስደነግጥ ድምፅ በጆሮው ነው፤በደኅንነቱም ሳለ ቀማኛ ይመጣበታል።
22 ፤ ከጨለማ ተመልሶ እንዲወጣ አያምንም፥ሰይፍም ይሸምቅበታል።
23 ፤ ተቅበዝብዞም። ወዴት አለ? እያለ እንጀራ ይለምናል፤የጨለማ ቀን እንደ ቀረበበት ያውቃል።
24 ፤ መከራና ጭንቀት ያስፈራሩታል፤ለሰልፍ እንደ ተዘጋጀ ንጉሥ ያሸንፉታል፤
25 ፤ እጁን በእግዚአብሔር ላይ ዘርግቶአልና፥ሁሉንም በሚችል አምላክ ላይ ደፍሮአልና፥
26 ፤ በደንዳና አንገቱና በወፍራሙ በጋሻውጕብጕብ እየሠገገ ይመጣበታልና፥
27 ፤ በስብም ፊቱን ከድኖአልና፥ስቡንም በወገቡ ላይ አድርጓልና፥
28 ፤ በተፈቱም ከተሞች ውስጥ፥ሰውም በሌለባቸው፥ክምር ለመሆን በተመደቡ ቤቶች ውስጥ ተቀምጦአልና
29 ፤ ባለጠጋ አይሆንም፥ ሀብቱም አይጸናም፤ጥላውንም በምድር ላይ አይጥልም፤
30 ፤ ከጨለማ አይወጣም፤ነበልባሉም ቅርንጫፎቹን ያደርቃቸዋል፥አበባዎቹም ይረግፋሉ።
31 ፤ ዋጋው ከንቱ ነገር ይሆናልናራሱን እያሳተ በከንቱ ነገር አይታመን።
32 ፤ ቀኑ ሳይደርስ ጊዜው ይፈጸማል፥ቅርንጫፉም አይለመልምም።
33 ፤ እንደ ወይን ያልበሰለውን ዘለላ ያረግፋል፤እንደ ወይራ አበባውን ይጥላል።
34 ፤ የዝንጉዎች ጉባኤ ሁሉ ለጥፋት ይሆናል፥የጉቦ ተቀባዮችንም ድንኳን እሳት ትበላለች።
35 ፤ ጉዳትን ይፀንሳሉ፥ በደልንም ይወልዳሉ፥ሆዳቸውም ተንኰልን ያዘጋጃል።