መጽሐፈ ኢዮብ።. Chapter 8

1 ፤ ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ።
2 ፤ እስከ መቼ ይህን ትናገራለህ?የአፍህስ ቃል እስከ መቼ እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናል?
3 ፤ በውኑ እግዚአብሔር ፍርድን ያጣምማልን?ሁሉንም የሚችል አምላክ ጽድቅን ያጣምማልን?
4 ፤ ልጆችህ በድለውት እንደ ሆነ፥እርሱ በበደላቸው እጅ ጥሎአቸዋል።
5 ፤ እግዚአብሔርን ብትገሠግሥ፥ሁሉንም የሚችለውን አምላክ ብትለምን፥
6 ፤ ንጹሕና ቅን ብትሆን፥በእውነት አሁን ስለ አንተ ይነቃል፥የጽድቅህንም መኖሪያ ያከናውንልሃል።
7 ፤ ጅማሬህ ታናሽ ቢሆንም እንኳፍጻሜህ እጅግ ይበዛል።
8 ፤9፤ ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ነውናእኛ የትናንት ብቻ ነን፤ ምንም አናውቅም፤ስለዚህ የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፥አባቶቻቸውም ለመረመሩት ነገር ትጋ፤
10 ፤ እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፥ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?
11 ፤ በውኑ ደንገል ረግረግ በሌለበት መሬት ይበቅላልን?ወይስ ቄጠማ ውኃ በሌለበት ቦታ ይለመልማልን?
12 ፤ ገና ሲለመልም ሳይቈረጥም፥ከአትክልት ሁሉ በፊት ይደርቃል።
13 ፤ እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ ፍጻሜአቸው እንዲሁ ነው፤የዝንጉም ሰው ተስፋ ይጠፋል።
14 ፤ ተስፋው ይቈረጣል፥እምነቱም እንደ ሸረሪት ቤት ይሆናል።
15 ፤ ቤቱን ይደግፈዋል፥ አይቆምለትም፤ይይዘውማል፥ አይጸናለትም።
16 ፤ ፀሐይም ሳይተኵስ ይለመልማል፥ጫፉም በአታክልቱ ቦታ ይወጣል።
17 ፤ በድንጋይ ክምር ላይ ሥሩ ይጠመጠማል፤የድንጋዮቹን ቦታ ይመለከታል።
18 ፤ ከቦታው ቢጠፋ።አላየሁህም ብሎ ይክደዋል።
19 ፤ እነሆ፥ የመንገዱ ደስታ እንዲህ ነው፤ሌሎችም ከመሬት ይበቅላሉ።
20 ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር ፍጹሙን ሰው አይጥለውም፥የኃጢአተኞችንም እጅ አያበረታም።
21 ፤ አፍህን እንደ ገና ሳቅ ይሞላል፥ከንፈሮችህንም እልልታ ይሞላል።
22 ፤ የሚጠሉህ እፍረት ይለብሳሉ፤የኃጢአተኞችም ድንኳን አይገኝም።