ኦሪት ዘዳግም. Chapter 32
1 ፤ ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔም እናገራለሁ፤ምድርም የአፌን ቃሎች ትስማ።
2 ፤ ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትፈስሳለች፥ነገሬ እንደ ጠል ትንጠባጠባለች፤በልምላሜ ላይ እንደ ጤዛ፥በሣርም ላይ እንደ ካፊያ።
3 ፤ የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁና፤ለአምላካችን ታላቅነትን ስጡ።
4 ፤ እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው፤መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤የታመነ አምላክ፥ ክፋትም የሌለበት፥እርሱ እውነተኛና ቅን ነው።
5 ፤ እነርሱ ረከሱ፤ ልጆቹም አይደሉም፤ነውርም አለባቸው፤ ጠማማና ገልበጥባጣ ትውልድ ናቸው።
6 ፤ ደንቆሮ ብልሃተኛም ያልሆንህ ሕዝብ ሆይ፥ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ?የገዛህ አባትህ አይደለምን?የፈጠረህና ያጸናህ እርሱ ነው።
7 ፤ የዱሮውን ዘመን አስብ፥የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፤አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል።
8 ፤ ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን ባወረሰ ጊዜ፥የአዳምን ልጆች በለየ ጊዜ፥እንደ እስራኤል ልጆች ቍጥርየአሕዛብን ድንበር አቆመ።
9 ፤ የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ሕዝቡ ነው፤ያዕቆብም የርስቱ ገምድ ነው።
10 ፤ በምድረ በዳ በጥማት፥የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤ከበበው ተጠነቀቀለትም፤እንደ ዓይን ብሌን ጠበቀው።
11 ፤ ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፥ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፥በክንፎቹም አዘላቸው።
12 ፤ እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም።
13 ፤ በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፤የእርሻውን ፍሬ በላ፤ከዓለትም ድንጋይ በሚገኝ ማር፥ከጭንጫውም ድንጋይ በሚገኝ ዘይት አጠባው፤
14 ፤ የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውም ወተት፥ከጠቦት ስብ ጋር፥የባሳንንም አውራ በግ፥ ፍየሉንም፥ከስንዴ እሸት ጋር በላህ፤ከወይኑም ደም ያለውን ጠጅ ጠጣህ።
15 ፤ ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤የፈጠረውንም እግዚአብሔርን ተወ፤የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ።
16 ፤ በሌሎች አማልክት አስቀኑት፥በርኵሰታቸውም አስቈጡት።
17 ፤ እግዚአብሔር ላልሆኑ አጋንንት፥ለማያውቋቸውም አማልክት፥በቅርብ ጊዜ ለተነሡ ለአዲሶችአባቶቻቸውም ላልፈሩአቸው አማልክት ሠዉ።
18 ፤ የወለደህን አምላክ ተውህ፥ያሳደገህን እግዚአብሔርን ረሳህ።
19 ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ስላስቈጡትእግዚአብሔር አይቶ ጣላቸው።
20 ፤ እርሱም አለ። ፊቴን እሰውርባቸዋለሁ፤ፍጻሜያቸው ምን እንደ ሆነ አያለሁ፤ጠማማ ትውልድ፥ያልታመኑም ልጆች ናቸው።
21 ፤ አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤
22 ፤ እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፥ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፥የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።
23 ፤ መከራን እጨምርባቸዋለሁ፤በፍላጾቼም እወጋቸዋለሁ።
24 ፤ በራብ በንዳድ ይጠፋሉ፤በንዳድና በመራራ ጥፋት ያልቃሉ፤የአራዊትን ጥርስ፥የምድርንም እባብ መርዝ እሰድድባቸዋለሁ።
25 ፤ ጕልማሳውን ከድንግል፥ ሕፃኑንም ከሽማግሌ ጋር፥በሜዳ ሰይፍ፥ በቤትም ውስጥ ድንጋጤ ያጠፋቸዋል።
26 ፤ እበትናቸዋለሁ አልሁ፤ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ።
27 ፤ ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ።እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂእግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገምእንዳይሉ፥ስለ ጠላቱ ቍጣ ፈራሁ።
28 ፤ ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፥ማስተዋልም የላቸውም።
29 ፤ አእምሮ ቢኖራቸው፥ይህንን ያስተውሉ ነበር፥ፍጻሜያቸውንም ያስቡ ነበር።
30 ፤ እርሱ አምላካቸው ካልሸጣቸው፥እግዚአብሔርም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥አንድ ሰው እንዴት ሺህን ያሳድድ ነበር?ሁለቱሳ እንዴት አሥሩን ሺህ ያሸሹ ነበር?
31 ፤ አምላካችን እንደ አማልክቶቻቸው አይደለም፤ጠላቶቻችንም ሰነፎች ናቸው።
32 ፤ ወይናቸው ከሰዶም ወይን፥ከገሞራም እርሻ ነው፤ፍሬያቸው ሐሞት ነው፤ዘለላውም መራራ ነው።
33 ፤ የወይን ጠጃቸው የእባብ መርዝ፥የእፉኝትም ሥራይ ነው።
34 ፤ ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ የለምን?በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን?
35 ፤ የጥፋታቸው ቀን ቀርቦአልና፥የሚመጣባቸውም ነገር ይፈጥናልናእግራቸው ሲሰናከልበቀልና ፍርድ የእኔ ነው።
36 ፤ ኃይላቸውም እንደ ደከመ፥የተዘጋ የተለቀቀም እንደሌለ ባየ ጊዜእግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፥ስለ ባሪያዎቹም ያዝናል።
37 ፤ እርሱም ይላል። አማልክቶቻቸው የት ናቸው?ይታመኑባቸው የነበሩት አማልክት?
38 ፤ የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፥የመጠጥ ቍርባናቸውንም የወይን ጠጅ የጠጡ?እነርሱ ይነሡ፥ ይርዱአችሁም፥መጠጊያም ይሁኑላችሁ።
39 ፤ አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ፤እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ከእጄም የሚያድን የለም።
40 ፤ እጄን ወደ ሰማይ እዘረጋለሁና፥እንዲህም እላለሁ። ለዘላለም እኔ ሕያው ነኝና
41 ፤ የሚንቦገቦግ ሰይፌን እስለዋለሁ፥እጄም ፍርድን ትይዛለች፥ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፥ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እከፍላለሁ።
42 ፤ ከተወጉት ከተማረኩትም ደም፥ፍላጾቼን በደም አሰክራለሁ፤ከጠላት አለቆችም ራስሰይፌ ሥጋ ይበላል።
43 ፤ የባሪያዎቹን ደም ይበቀላልና፥ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋልና፥ምድሪቱንና ሕዝቡን ይክሳልናእናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ።
44 ፤ ሙሴም የነዌም ልጅ ኢያሱ የዚህችን መዝሙር ቃሎች ሁሉ በሕዝቡ ጆሮ ተናገሩ።
45 ፤ ሙሴም ይህን ቃል ሁሉ ለእስራኤል ሁሉ ተናግሮ ፈጸመ።
46 ፤ እርሱም እንዲህ አላቸው። የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዝዙበት ዛሬ የምመሰክርላችሁን ቃል ሁሉ በልባችሁ አኑሩት።
47 ፤ ይህ ነገር ሕይወታችሁ ነው እንጂ ለእናንተ ከንቱ አይደለምና፤ በዚህም ነገር ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር ረጅም ዘመን ትቀመጣላችሁ።
48 ፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።
49 ፤ ወደዚህ በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ምድር በዓባሪም ተራራ ውስጥ ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፥ ለእስራኤልም ልጆች ርስት አድርጌ የምሰጣቸውን የከነዓንን ምድር እይ፤
50 ፤ ወንድምህም አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ ወደ ወገኖቹም እንደ ተከማቸ፥ በወጣህበት ተራራ ሙት፥ ወደ ወገኖችህም ተከማች፤
51 ፤ በእስራኤል ልጆች መካከል በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ባለው በመሪባ ውኃ ስለ በደላችሁኝ፥ በእስራኤልም ልጆች መካከል ስላልቀደሳችሁኝ፥
52 ፤ ምድሪቱን ፊት ለፊት ታያለህ እንጂ ወደዚያች እኔ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር አትገባም።