ኦሪት ዘዳግም. Chapter 33
1 ፤ የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ሳይሞት የእስራኤልን ልጆች የባረከባት በረከት ይህች ናት።
2 ፤ እንዲህም አለ።እግዚአብሔር ከሲና መጣ፥በሴይርም ተገለጠ፤ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥ከአእላፋትም ቅዱሳኑ መጣ፤በስተ ቀኙም የእሳት ሕግ ነበረላቸው።
3 ፤ ሕዝቡንም ወደዳቸው፤ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ናቸው፤በእግሮችህም አጠገብ ተቀመጡ፤ቃሎችህን ይቀበላሉ።
4 ፤ ሙሴ ለያዕቆብ ጉባኤ ርስት የሆነውንሕግ አዘዘን።
5 ፤ የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶችሁሉ ጋር በተከማቹ ጊዜ፥ንጉሥ በይሹሩን ነበረ።
6 ፤ ሮቤል በህይወት ይኑር፥ አይሙት፤ሰዎቹም በቍጥር ብዙ ይሁኑ።
7 ፤ የይሁዳ በረከት ይህ ነው፤ እንዲህም አለ።አቤቱ፥ የይሁዳን ድምፅ ስማ፥ወደ ወገኖቹም አግባው፤እጆቹ ይጠንክሩለት፤በጠላቶቹ ላይ ረዳት ትሆነዋለህ።
8 ፤ ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፥ቱሚምህና ኡሪምህ ለቅዱስህ ሰው ነው፥በማሳህ ለፈተንኸው፥በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፤
9 ፤ ስለ አባቱና ስለ እናቱ። አላየሁም ላለ፥ወንድሞቹንም ላላስተዋለ፥ልጆቹንም ላላወቀ፤ቃልህን አደረጉ፥ቃል ኪዳንህንም ጠበቁ።
10 ፤ ፍርድህን ለያዕቆብ፥ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ፤በፊትህ ዕጣንን፥በመሠዊያህም የሚቃጠል መሥዋዕት ይሠዋሉ።
11 ፤ አቤቱ፥ ሀብቱን ባርክ፥የእጁንም ሥራ ተቀበል፤የሚነሣበትን ወገብ ውጋው፥የሚጠሉትም አይነሡ።
12 ፤ ስለ ብንያምም እንዲህ አለ።በእግዚአብሔር የተወደደ በእርሱዘንድ ተማምኖ ይኖራል፤ቀኑን ሁሉ ይጋርደዋል፥በትከሻውም መካከል ያድራል።
13 ፤ ስለ ዮሴፍም እንዲህ አለ፥ምድሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተባረከ ይሁን፤በሰማያት ገናንነት በጠል፥በታችኛውም ቀላይ፥
14 ፤ በፀሐዩ ፍሬያት ገናንነት፥በጨረቃውም መውጣት ገናንነት
15 ፤ በቀደሙትም ተራሮች ከፍተኛነት፥በዘላለሙም ኮረብቶች ገናንነት፥
16 ፤ በምድሪቱም ገናንነትና ሞላዋ፥በቍጥቋጦው ውስጥ ከነበረው በረከትበዮሴፍ ራስ ላይ፥ ከወንድሞቹም በተለየው ራስ አናት ላይ ይውረድ።
17 ፤ ለላሞች በኵር ግርማ ይሆናል፤ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፤በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትንአሕዛብ ሁሉ ይወጋል፤የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።
18 ፤ ስለ ዛብሎንም እንዲህ አለ። ዛብሎን ሆይ፥ በመውጣትህ፥ይሳኮር ሆይ፥ በድንኳንህ ውስጥ ደስ ይበላችሁ።
19 ፤ የተሰወረውን የአሸዋውን መዝገብ፥የባሕሩንም ባለጠግነት ይጠባሉናአሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤በዚያ የጽድቅ መሥዋዕት ይሠዋሉ።
20 ፤ ስለ ጋድም እንዲህ አለ።ጋድን ሰፊ ያደረገ ቡሩክ ይሁን፤እንደ አንበሳይቱ ዐርፎአል፤ክንድንና ራስን ይቀጠቅጣል።
21 ፤ በዚያ የአለቃ እድል ፈንታ ቀርቶአልናየመጀመሪያውን ክፍል ለራሱ መረጠ፤ወደ ሕዝብ አለቆችም መጣ፤የእግዚአብሔርንም ጽድቅ፥ፍርዱንም ከእስራኤል ጋር አደረገ።
22 ፤ ስለ ዳንም እንዲህ አለ።ዳን የአንበሳ ደቦል ነው፤ከባሳን ዘልሎ ይወጣል።
23 ፤ ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ።ንፍታሌም በሞገስ ጠግቦአል፥የእግዚአብሔርንም በረከት ተሞልቶአል፤ባሕሩንና ደቡቡን ይወርሳል።
24 ፤ ስለ አሴርም እንዲህ አለ።አሴር በልጆች የተባረከ ይሁን፤በወንድሞቹ የተወደደ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ።
25 ፤ ጫማህ ብረትና ናስ ይሆናል፤እንደ ዕድሜህ እንዲሁ ኃይልህ ይሆናል።
26 ፤ ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድእንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም።
27 ፤ መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ።አጥፋው ይላል።
28 ፤ እስራኤልም ተማምኖ፥የያዕቆብም ምንጭ ብቻውን፥እህልና የወይን ጠጅ ባለባት ምድር ይኖራል፤ሰማያቱም ጠልን ያንጠባጥባሉ።
29 ፤ እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፤በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው?እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው።ጠላቶችህም ይገዙልሃል፤አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።